በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የተካሄዱ በርካታ የጥናትና ምርምር ውጤቶች ተግባር ላይ መዋላቸው ተገለጸ

ሰኔ 21/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ በዘርፉ ከተሰሩ ችግር ፈች ጥናትና ምርምሮች ውስጥ ከ80% በላይ የሚሆኑት ተግባር ላይ እንደዋሉ ገለጹ፡፡

ኢንስቲትዩቱ አምራች ኢንዱስትሪዎች በጥናትና ምርምር እንዲደገፉ የጥናትና ምርምር የአሰራር መመሪያ ስላዘጋጀ በየማዕከሉ የሚሰሩ ጥናትና ምርምር ስራዎች ለፖሊሲ ቀረፃና ለአምራች ኢንዱስትሪው ልማት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በችግር ፈች የጥናትና ምርምር ስራዎች በመደገፋቸው ምክንያት ቀደም ሲል በጥቂት ምርቶች ላይ ተመርኩዞ የነበረው ኤክስፖርታችን አሁን በርካታ የምርት ስብጥሮችን እንዳካተተ ተናግረዋል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት የአቅም ልማት ስትራቴጅ መዘጋጀቱን የገለፁት ዶ/ር ሚልኬሳ በ2017 ዓ.ም 52 ችግር ፈች የጥናትና ምርምር ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post