የስሚንቶ ፋብሪካዎች የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረምን በሰፊው መጠቀም ከቻሉ የውጭ ምንዛሬ ብክነትን በከፍተኛ ደረጃ ማስቀረት ይቻላል (አቶ ሀርቢ ቡህ)
ሰኔ 22/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የስሚንቶ ፋብሪካዎች በናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የተጀመረውን የባዮ ማስ አጠቃቀም በስፋት መጠቀም ከቻሉ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በከፍተኛ ደረጃ ማስቀረት እንደ ሚቻል ገለጹ፡፡
በፕሮሶፒስ ጁሊ ፍሎራ አረምን በሀይል አማራጭነት መጠቀምን አስመልክቶ በተካሄደው የልምድ ልውውጥ መድረክ የተሳተፉት አቶ ሀርቢ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ከተማዋን የአምራች ኢንዱስትሪ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ታስቦ እየተሰራ እንደሆነና በከተማ አስተዳደሩ ስር ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም 61.8% መድረሱን ተናግረዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ከተኪ ምርት አንጻር በከተማ አስተዳደሩ ያሉ ስልሳ ዘጠኝ ፋብሪካዎች ሀገር በቀል ምርቶችን በግብአትነት እየተጠቀሙ እንዳለና ዘጠኝ ፋብሪካዎችም የኤክስፖርት ስራ መጀመራቸውን አስረድተዋል፡፡
ከአጠቃላይ የልማት ዘርፎች የአምራች ኢንዱስትሪው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ከስራ ዕድል ፈጠራ አኳያ ሁለተኛ ደረጃን ይይዛል ያሉት አቶ ሀርቢ በድሬዳዋ ከተማ ለሀያ አራት ሽ ስድስት መቶ ዜጎች የስራ ዕድል መፈጠሩን አብራርተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት