አምራች ኢንዱስትሪዎችን የኤክስፖርት አፈፃፀም የበለጠ ለማሻሻል ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ይደረጋል። (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

መስከረም 8/2018 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ ዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤክስፖርት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስሉ ጋር ተቀናጅቶ ድጋፍና ክትትሉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

አቶ ታረቀኝ በሀምሌና በነሀሴ ወር አዳዲስ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ኤክስፖርት ስራ መግባታቸው እንደ ሀገር ያለን የኤክስፖርት አፈፃፀም ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ አድርጓል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ሚኒስትር ደኤታው በኤክስፖርት አፈፃፀማቸው ከመቶ ፐርሰንት በላይ ለሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዕውቅና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጠው መንግስታዊ ድጋፍ የኤክስፖርት ዕቅዳቸውን ከማሳካት አኳያ ያላቸውን የአፈፃፀም አቅም መሰረት ያደረገ እንደሚሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሽ ለማ ገልፀዋል፡፡

Share this Post