በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በነሀሴ ወር ኤክስፖርት በተደረጉ ምርቶች 35.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተመዘገበ።

መስከረም 8/2018 ዓ.ም (ኢ.ሚ) ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኤክስፖርት አፈፃፀማቸው ከተሻሉ 60 አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር የሁለት ወራት የኤክስፖርት አፈፃፀም የግምገማ መድረክ አካሄደ፡፡

በመርሀ ግብሩ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የኤክስፖርት አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረበው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የወጭ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አበበ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በነሀሴ ወር ኤክስፖርት በተደረጉ ምርቶች 35.1 ሚሊዮን ዶላር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የሀምሌንና ነሀሴ ወርን የኤክስፖርት አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን የሁለት ወራት አፈፃፀም 68.1 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደተገኘ አብራርተዋል፡፡

ቀደም ሲል አምራች ኢንዱስትሪዎች ያነሱት የነበረው የሀይል አቅርቦት ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተቀረፈ መምጣቱን ተሳታፊዎች በመርሀ ላይ ግብሩ የተሳተፉ የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡

Share this Post