ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 408 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ቀረበ፡፡

ህዳር 8/2018 ዓ.ም (ኢሚ) በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 408 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች መቅረብ መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ ገለፁ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ለኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት አቅርቧል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በወቅቱ ባቀረቡት ሪፖርት፤ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 82 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለማቅረብ ታቅዶ 408 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማቅረብ ተችሏል ብለዋል፡፡

መለዋወጫ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ስጥ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ የውጪ ምንዛሬው ለጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ለቆዳ፣ ለምግብና መጠጥ፣ ለኬሚካልና ኮንስትራክሽን፣ ለማኒፋክቸሪግ፣ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች መቅረቡን ተናግረዋል፡፡

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው፤ የባንኮች ተቀማጭ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ የአምራች ዘርፉ የስራ ማስኬጃ ፍላጐት በብድር መሟላቱ ለውጭ ምንዛሬ አቅርቦቱ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከቱን አመላክተዋል፡፡

Share this Post