የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም 59 በመቶ ደርሷል(የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ )
የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የተፈጠረ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ ተቋማዊ አደረጃጃት እንዲኖረው በማድረግ በተሰራ ስራ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አጠቃቀም 59 በመቶ እንዲደርስ ማድረግ መቻሉን አዲሱ የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ገልጸዋል፡፡