ባለፉት ስድስት ወራት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 52.87 ከመቶ ማድረስ ተችሏል

ጥር 30/2015ዓ.ም (ኢ.ሚ) በ2015 በጀት አመት የመጀመሪያው ስድስት ወር የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም 55.5 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 52.87 በመቶ ማድረስ ተቻለ፡፡ ይህም ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 46.2 በመቶ ጋር ሲነፃፀር የ6.67 በመቶ መሻሻል በማምጣት ወደ 52.87 በመቶ ማደግ ችሏል፡፡

ይህን አፈፃፀም በየንዑስ ዘርፉ ሲታይ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪዎች 61.71 በመቶ ፣የቆዳ አምራች ኢንዱስትሪዎች 57.52 በመቶ ፣የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች 57 በመቶ ፣የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንዱ/ሪዎች 59 በመቶ ፣የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪዎች 29.12 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡

የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 52.87 በመቶ ለማድረስ ለ2,611 የኢንዱስትሪ ሰራተኞችና አመራሮች ስልጠና በመስጠት የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የሰው ኃይል አቅም የማጎልበት ስራ ተሰርቷል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

Share this Post